13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Sunday, December 11, 2011

ታላቅ ዜና ቤተክርስቲያን


“ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው።” መዝ. 65፡ 5
ታላቅ ዜና ቤተክርስቲያን

ቀዳማዊ ዜና
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲዯን

በንብ የሚጠበቀው የቦሌ በሻሌ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወአቡነ ሠላማ ቤተክርስቲያን በሕዳር 12 / 2002 ዓ.ም ለሚከበረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በዋዜማው ሕዳር 11 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ዋዜማ ቆመው ሳለ ከምስራቅ አቅጣጫ አውራውን አስቀድሞ እየተመመ የመጣው የንብ መንጋ ቤተክርስቲያኗን ዞሮ ጣራዋ ሸራ ግድግዳዋ ሳጠራ ወደሆነችው ቤተመቅደሷ ብቻ በተሰራው (ቅድስት እና ቅኔ ማኅሌት የሌለው አነስተኛ መጠን ያላት ቤተክርስቲያን ላይ) የቃልኪዳኑ ታቦተ ሕግ ባረፈበት መንበር ውስጥ መንጋው ንብ ገብቶ ሰፍሯል። የንቡ መንጋ ወደ መንበሩ ሲገባ በአገልግሎት ላይ ያሉትን ካህናት ሳይነካ አገልግሎቱም ሳይታጎል አድሯል። በሕዳር 12 ቀን 2002 ዓ.ም ምንም እንኳን ካህናቱ ስጋት ቢገባቸውም ታቦተ ሕጉን ማውጣት ግዴታ ነውና አስፈላጊው ስርዓተ አምልኮ ከተፈፀመ በኋላ ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ሲወጣ የንቡም ሠራዊት ከመንበሩ በምስራቅ በኩል በመውጣት ከምዕመናኑ ጋር ታቦቱን በማክበር ተመልሶ ወደ መንበሩ ሰፍሯል። ይህንንም ድንቅ ሥራ የተመለከቱ ምዕመናንም እግዚአብሔርን አመስግነዋል። አሁንም ይህ የንብ መንጋ በመንበሩ ውስጥ ይገኛል።  የንቡ መንጋ በሚሰራው ማር ብዙ ምዕመናን እየተፈወሱና ታላላቅ ተዓምራት እየተደረገላቸው ይገኛል።

ከእነዚህም ውስጥ፡-
v  በከባድ የራስ ምታት በሽታ  (ማይግሬን) ለ15 ዓመታት ሲሰቃዩ የነበሩ አንድ ምዕመን ከመንበሩ ውስጥ በወጣችው አንድ ንብ ራሳቸውን ተነድፈው ድነዋል።
v  በእብድ ውሻ ተነድፎ ይሰቃይ የነበረ አንድ ክርስቲያን ወንድም በህክምና ማዕከሉ የውሻውን አንገት ካላመጣህ ልትድን አትችልም ተብሎ እየተሰቃየ ሳለ ወደ እዚሁ ቤ/ክ መጥቶ በጸሎት ላይ እንዳለ ከመቅደሱ የወጡ ሁለት ንቦች ውሻው የነከሰበትን ቦታ ቢነድፉት ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ድኗል።
v  አንዲት ምዕመን ለ5 ዓመታት ያህል በአእምሮ በሽታ አብዳ ቤተሰቦቿን የማታውቅ የነበረች ከማሩ ጸበል ወስደው ቢያጠጧት በ5ኛው ቀን ድና ምስክርነት ሰጥታለች።
v  በኪንታሮት በሽታ ለብዙ ዘመናት ሲሰቃይ የነበሩ ምዕመን ከመንበሩ የተቆረጠውን ማር ተቀብተው ድነዋል።
v  ለብዙ ጊዜ መስማት ተስኖት የነበረ ምዕመን ማሩን በጥብጦ በጆሮው ውስጥ ቢጨምር ወዲያው ድኖ መስማት ችሏል።
v  እጅና እግሯ ሲንቀጠቀጥ የነበረች ሴት በፀሎት ላይ ሳለች በአንድ ንብ ተነድፋ ወዲያውኑ ከበሽታዋ ድናለች።
v  ለብዙ ዓመታት በአልጋ ቁራኛ ተይዛ ትኖር የነበረች ሴት ከማሩ ጸበል ወስደው ቢያጠጧትና ሰውነቷን ቢቀባቧት ወዲያውኑ ድና ከሰው ድጋፍ በመላቀቅ በእግሯ መጥታ መስክራለች።
v  በአስም፣ በጨጓራ፣ በኩላሊት፣ በደም ግፊት፣ በጭንቀት በሽታ ሲሰቃዩ የነበሩ ምዕመናንም የማሩን ጸበል ጠጥተው ድነው ምስክርነታቸውን መስጠታቸውንና በዚህ አነስተኛ ጽሑፍ ያልተገለጹ ብዙ ገቢረ ተዓምራትና ፈውሶች ተደርገዋል።
አዲስ ዜና

አዲሷ ቤተልሔም
በሕዳር (ልብ ይበሉ ሁለቱም ታላላቅ ዜናዎች የተፈጸሙባቸው ወር አንድ ናቸው “ወርሐ ሕዳር”) በዕለተ ሐሙስ ሕዳር 21 ቀን 2004 ዓ.ም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የሆነችው ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ድል አድርጋ በክብር የተመለሰችበትን በዓል በሚከበርበት ዕለት ካህናት በጸሎተ ቅዳሴ ላይ ሳሉ ከቀኑ 7፡30 ከየት መጣ ተብሎ የማይታወቅ እጅግ ብዙ የሆነ የንብ መንጋ ዳግም ወደዚህች ቤተክርስቲያን መጣ። ድምፁ ያስደነገጣቸው ቀዳስያን ካህናት እና ምዕመናን ምን መጣ? ወይስ የመንበሩ ንቦች ወጡን? በማለት ሲደናገጡ ከዲያቆናት መካከል አንዱ ወጥቶ ቢመለከት ንቡ በቤ/ክኑ ጉልላት ላይ የመስቀል ምልክት ሰርቶ በጣራው ላይ ሲያርፍ የቀረው ንብ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ይዞራል። “በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ፡ እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት” እንዳለ እጹብ ከማለት በቀር ምን ማለት ይቻላል? ይህም የንብ መንጋ ሥርዓተ ቅዳሴው ሲያበቃ አዲስ በተሰራችው፣ በመጠኗ አነስተኛ የሆነችው ቤተልሔም ውስጥ ገብቶ ሰፍሯል። ከደብሩ አገልጋይ ካህናት ውስጥ አንዱ ቄስ ገብተው ሲያጥኑና የንቡን ሁኔታ ሲመለከቱ ከመግባቱ ገና በ10ኛ ቀኑ ማር ለመስራት የሚያስፈልገውን የመጀመሪያ ደረጃ እንደጀመረ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ሲራክ ገበየሁ በታሕሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በተዘጋጀው ልዩ መርሐ ግብር ላይ ለምዕመናን ተናግረዋል።

“ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” (ት. ሐጌ. 1፡ 8)
ይህች ቅድሰት ቤተክርስቲያን እጅግ ብዙ የሆነ ገቢረ ተዓምራትን እያደረገች የምትገኝ የሠማይ ደጅ ናት። ገና ብዙ ሕዝበ ክርስቲያንም ታላላቅ ተዓምራትና ፈውሶች የሚያገኙባት ስለሆነች ከሁሉ በፊት በጸሎት፣ በሃሳብ፣ በጉልበት፣ በገንዘብ የበኩሎን ክርስቲያናዊ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉልን በቅድስት ቤ/ክ ስም እየጠየቅን፤ እግዚአብሔር ባሉበት ቦታ በሠላምና በጤና እስከቤተሰብዎ እንዲጠብቅዎ ዘወትር በጸሎት እያሰብን፤ ቢችሉ ወደ ቦታው ድረስ በመምጣት እንዲያዩ፤ ባይችሉ በመደወል አስፈላጊውን መረጃ በሰፊው ማግኘት ይችላሉ። አሁን ቤተክርስቲያኗ ምን ያስፈልጋታል?
አሁን ያለው ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያንን መስራት፡ አሁን ያለችው ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በቆርቆሮ የተሰራች ሲሆን ይህም የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ከነበረችበት ሸራና ሳጠራ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ለብሳለች ፤ እንዲሁም ካህናት ቅኔ ማኅሌት የሚቆሙበት፣ ምዕመናን የሚያስቀድሱበትና ክቡር ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚቀበሉበት ግድ በመሆኑ ከመቅደሱ ተቀጥሎ በፎቶው ላይ እንደምታዩት ቆርቆሮ የለበሰ ቅኔማኅሌትና ቅድስት ተሰርቷል። ይህ ግን ለዘለቄታው የሚሆን ሳይሆን ለጊዜው ለአገልግሎቱ ተብሎ ነው። ለዘለቄታው ግን ቋሚ ቤተክርስቲያን መስራቱ ግድ ነው። ይህንንም የደብሩ ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።


አዲስ ለመስራት የታሰበው ቤተክርስቲያን ዲዛይን

ለበሻሌ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ
1
ሲሚንቶ
340 ኩንታል
2
አሸዋ
79 ሜትር ኩብ
3
ጠጠር
46 ሜትር ኩብ
4
ድንጋይ
30 ሜትር ኩብ
5
ብሎኬት
2592 በቁጥር
6
የብረት መስኮት
1.8 x 4.75 (8.55 ካሬ)= 3 በቁጥር


0.9 x2.5 (2.25ካሬ) =10 በቁጥር


0.8 x1.9 (1.52ካሬ)= 7 በቁጥር


1.2 x1.4 (1.68ካሬ) =3 በቁጥር
7
መስታወት
76 ካሬ ሜትር

1. ቀለም ስራ እስቱኮ
36 ኪሎ

2. ግሎ
8 ኪሎ

3. ቀለም 
112 ሊትር

4. ጂፕሰም
18 ኪሎግራም
8
የእንጨት በር
0.9 x2.5= 3በቁጥር

1.2 x2.6
1በቁጥር
9
ቆርቆሮ ጣሪያ
252 በቁጥር
10
አሸንዳ
90 ሜትር
11
1. ባህር ዛፍ አጠና (10-12)
20 በቁጥር

2. ምስማር
5 ኪሎግራም
12
ባህር ዛፍ ውቅረት


1. አጠና (8-10)
32 በቁጥር

2. ምስማር
7ኪሎግራም

3. ሞራሌ (5x7)
37 በቁጥር

4. ምስማር
3 ኪሎግራም
13
ከፈፍ ጣውላ


1. ጣውላ
36 በቁጥር

2. ምስማር
12 ኪሎግራም
14
ኮርኒስ


1. ሞራሌ(5x5)
300

2. ቺፕውድ
280 ካሬ ሜትር 100 በቁጥር

3. ምስማር(6 cm)
18 ኪሎግራም

4. ምስማር (3cm)
18 ኪሎግራም
15
ወለል
ሊሾ 225 ሜትር ካሬ
16
ቶንዲኖ ብረት (ፌሮ)
6 =136 ኪሎግራም


8= 442 ቤርጋ


10= 4 ቤርጋ


12 =132 ቤርጋ


14= 49 ቤርጋ


16= 38 ቤርጋ


20=12 ቤርጋ

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡ 0911563714 (መልዓከ ፀሐይ ሲራክ የቤተክርስቲያኗ ዋና አስተዳዳሪ) ይደውሉ።
የባንክ አካውንት፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ፡ 0173012096600 የቦሌ በሻሌ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን
“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን።” ነህ.2፡20
ምንጭ፡ የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት ታሕሳስ 1/ 2004 ዓ.ም