13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Thursday, October 13, 2011

ይድረስ ለፈጣሪ

ይድረስ ለፈጣሪ መንበረ ጸባዖት
ከትልቁ ሥፍራ ከሰማዩ መንግሥት
ፍርድ ሳይዛነፍ ከሚፈጸምበት፡፡
 ላኪው በምድር ላይ ግፍ የደረሰብኝ
ጐስቋላ አገልጋይህ ደካማ ባሪያህ ነኝ፡፡

ሳጥናኤል የሚሉት የቀድሞ ጠላቴ
 ቂሙን ሳይዘነጋ እንደ አዳም አባቴ 
  ከገነት ሊያስቀረኝ ቀጥቅጦ ጥሎኛል።
ከመርዘኛው ባሕር በቁሜ ዘፍቆኛል።
በአፍና አፍንጫዬ ደግሞም በጆሮቼ
መርዙ ተጠቅጥቆ  በየአካል ክፍሎቼ
 አውጣኝ እያልኩህ ነው እባሕር ገብቼ፡፡
  ለመታገል ሞከርኩ ከእጁ አልወጣሁም።
ደካማ ነኝና በፍፁም አልቻልኩም።
ፍርድ ሰጭው ዳኛ ችግሬን ቃኝተኸው
   መፍትሔ እንድትሰጠኝ ወዳንተ እጮኻለሁ፡፡

                         ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን   1986  ዓም
                          /በሐመር መጽሔት ለንባብ የዋለ/ 
Source: http://kesisyaredgebremedhin.blogspot.com

No comments:

Post a Comment