13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Friday, October 21, 2011

ነገረ ቅዱሳን ክፍል 9 እና ዋቢ መጻሕፍት


አዋልድ መጻሕፍትን ማንበብ እንዲገባ የመጽሐፍቅዱስ ምስክርነት
አዋልድ መጻሕፍት ማለት የዐሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት ልጆች ናቸው። ዐሥራው የሚባለው መላው 81 ቅዱሳት መጻሕፍት ሲሆኑ አዋልድ የሚባሉትን ደግሞ ከዐሥራው መጻሕፍት የወጡ ወይም የተገኙ ዐሥራው መጻሕፍትን በማብራራት በመተርጎም በመተንተን የሚያገለግሉ ናቸው። ሁለቱም መጻሕፍት የቤተክርስቲያኗን ሃይማኖት ሥርዓት ወይም ትውፊት በመጠበቅ አንድነት አላቸው።
ለምሳሌ፡ ነቢዩ ሳሙኤል “የቀረው የሰሎሞን ነገር ያደረገውን ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ላይ ተጽፏል” (1ኛ ነገ.11፡41)፣ “የቀረውም የኢዮርብአም ነገር እንዴት እንደተዋጋ እንዴትም እንደነሠ እነሆ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል።”(1ኛ ነገ. 14፡19) በማለት የአዋልድ መጽሕፍትን መኖር ይገልጻል።
“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
2ኛ ጢሞ.3፡16 - 17

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ ድንግል፤ ወለመስቀሉ ክቡር
ከየካቲት/2003 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም


ዋቢ መጻሕፍት
1.      መጽሐፍቅዱስ
2.     መሠረታዊ የመጽሐፍቅዱስ አጠናን ዘዴ…. በመምህር ቸርነት አበበ (2003)
3.     መዝገበ ታሪክ 1 እና 2 …. በመምህር ኅሩይ ኤርምያስ (5ኛ እትም 2001)
4.     የቅዱሳን ታሪክ ቁጥር 5ኛ መጽሐፍ (1998 ዓ.ም)
5.     ነገረ ቅዱሳን (ነገቅ. 2000) …. በቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
6.     ፍኖተ ቅዱሳን… በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
7.     የመጽሐፍቅዱስ መዝገበ ቃላት
8.     ገድለ አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
9.     ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

No comments:

Post a Comment