13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Sunday, June 10, 2012

ዝክረ ቅዱሳን ዘወርሐ ሰኔ


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሰኔ 9 ሳሙኤል ነብይ

ሳሙኤል ማለት ሰማእኒ እግዚአብሄር ማለት ነው፡፡ 1ሳሙ፡20 አንድም ካህን ተአማኒ ማለት ነው።1ሳሙ 2፡35 ትውልዱ ከነገደ ኤፍሬም ነው፣አባቱ ህልቃና እናቱ ሃና ይባላሉ። የተወለደው የአርማቴም ዕዳ በሆነች በመሴፋ ሲሆን የብፅዓት ልጅ ነው።ጡት ሲተው እናቱ አፉ እህል ሳይለምድ ሆዱ ዘመድ ሳይወድ ወስዳ ለቤተእግዚአብሄር ሰታዋለች።
    ሊቀካህናቱ ዔሊ ካህናቱ አፍኒን ፊንሃስ ይባላሉ።አፍኒን ፊንሃስ ጽሃነ ምግባር ነበሩ ጌታ ዔሊን ልጆችህን ስራ ቅጻ አለው። እነሱ ተመክረው የማይመለሱ፣ ዔሊም ከእግዚአብሄር ይልቅ ለልጆቹ አድልቶ ከሹመታቸው ልሻራቸው ከመዓረጋቸው ላዋርዳቸው የማየል ቢሆን ጌታ አስቀድሞ በራዕይ አስታውቆ ቁጣውን በሞተ እስራኤል ጀምሮ በጼዋ ጽየን፣ በሞተ ዔሊ ፈጽሞ ሳሙኤልን ሊቀካህናት አድርጎ ሾመው።
         ክህነት ከምስፍና አንድ አድርጎ ይዞ 40 ዘመን አስተዳደራቸው አረጀ። ኢዩኤል አብያ የሚባሉ ሁለት ልጆች ነበሩት። ካህናት አድርጎ ሾማቸው። ደሃ የሚበድሉ ፍርድ የሚያጎድሉ ቢሆን እስራኤል “አንተስ ልህቀ ከመ ኢትመግበነ ወደቂቅከነ ኢሆሩ በፍኖትከ” አንተ እንዳታስተዳድረን አረጀህ ሸመገልህ፣ ልጆችህም አሰርህን አልተከተሉም በዚያውም ላይ በኢያቢስ ዘገለዓድ ባሉ ሁለት ነገድ ተኩል  ወንድሞቻችን ናዖስ አምናዊ ቀኝ ቀኝ አይናችሁን ገብሩልን ይላልና ቅን ፍርድ የሚፈርድልን ከጠላት የሚታደገን ንጉስ አንግስልን አሉት ጌታ ከሙስ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ካህናትን መሳፍንትን አስነሳ እንጂ እንደ አህዛብ ንጉስ አንግሶላአአዋለን ተው አይሆንም አላቸው ጌታ “ስምዖሙ ቃሎሙ ዘይቤሉከ-የሚሉህን ስማቸው” አለው። ሳዖል ወልደቂስን ቀብቶ አንግሶላቸዋል። ለእነርሱም እንዲገዙ ስርአት ሰርቶባቸዋል። ኋላም ሳዖል ቢበድል የእሴይ ልጅ ዳዊትን ቀብቶ አንግሶላቸዋል። ዳዊትን ከቀባ በኋላ  ጥቂት ጊዜ ቆይቶ በዚህ እለት አርፏል።
·         የነበረው በ1100 ዓ.ዓ ገደማ ነው።
ሰኔ11 ገላውዲዎስ ሰማዕት
  ገላውዲዎስ ማለት ዕንቆጳዘዮን ማለት ነው።ሃገሩ አንጾኪያ ነው። አባቱ አብጥልማዎስ የንጉስ ኑማርያኖስ ወንድም ነው። እንደ ዮሴፍ እስራኤላዊ መልከቀና እንደ ዮፍታሄ ፣ እንደ ጌዴዎን ሃይለኛ ነበረ። የሃገሩም ሰዎች ከመውደዳቸው የተነሳ ስዕሉን ስለው ከአደባባይ አቁመው ያደንቁለት ነበር።
   ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሃይማኖታችሁን ካዱ ለጣዖት ስገዱ እያለ ምዕመናንን ሲፈጅ እርሱ ከቅዱስ ፊቅጦር ጋር ለአንብቦ መጻህፍት ይተጋ ነበር። ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና በአምሳለ አረጋዊ መጥቶ ልጆች ይህ ንጉስ ምህረት የሌለው ጨካኝ እንደሆነ አታውቁምን አሁንም ቢሰማ ይጣላችኋልና መስላችሁ እደሩ አላቸው። በነገሩ ጠላትነቱን አውቀው ኦ አቡሃ ለሐሰት ረሃቅ እምኔነ ወግድልን አሉት አርአያውን ለውጦ በአምሳለ ገብር ፀሊም ሆኖ ባማችሁኝ አግኙኝ ብሏቸው ሄደ ንጉሱን ገላውዲዎስና ፊቅጦር ሳሉ መንግስትህ ይጸና መስሎሃልን አለው። ካሉበት አስጠርቶ ሃይማኖታችሁን ካዱ ለጣዖት ስገዱ አላቸው አይሆንም ይህን አናደርግም አሉት ከዛ እናዳይቀጣቸው ቤተሰቦቻቸውን ፈርቶ ፊቅጦርና ወደ እስክንድሪያ ሰደደው እርሱንም ወደ አንዲናው ላከው።
    የአንዲናው መስፍን አርያኖስ ምነው ወንድሜ ንጉስ የወደደውን ወደህ የጠላውን ጠልተህ በግዛትህ በሹመትህ ተደላድለህ አትኖርምን አለው። አንሰ ኢመጻዕኩ ኃቤከ ከመታስሕተኒ ነውን? አለው። ለማስፈራራትም ቢሉ ተቆጥቶም ነው ቢሉ የያዘውን ጦር ቢጥልበት ጎኑን ወግቶት በሰማዕትነት አርፏል።
·         ሰማዕትነት የተቀበለው በ304 ዓ.ም አካባቢ ነው።
የቅዱሳኑ በረከት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ለዘለዓለም ይኑር፤ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ ክፍል 2