13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Thursday, February 28, 2013

6ኛውን ፓትርያርክ ------ ብፁዕ አቡነ ማትያስ




የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ abune matyas 2ለመምረጥ በተደረገው ሂደት መሠረት 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ በመመረጥ  የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 70 ድምጽ በማምጣት ምርጫው ተጠናቋል፡፡     አንደ ድምፅ በትክክል ባለመሞላቱ ውድቅ ሆኗል፡፡

ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ማትያስ በመጨረሻ ባስተላለፉት መልእክት “ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋር አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሁናል ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የሚያገለግሉበት ጥበብ መንፈሳዊ ከዕድሜና ጤና ጋር ይስጥልን።

ስብሐት ለእግዚአብሔር

source: eotc-mkidusan.org