የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ
ለመምረጥ
በተደረገው ሂደት መሠረት 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ
ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ በመመረጥ የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው
ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98
ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 70 ድምጽ በማምጣት ምርጫው ተጠናቋል፡፡ አንደ ድምፅ በትክክል ባለመሞላቱ
ውድቅ ሆኗል፡፡
ፓትርያርክ
ሆነው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ማትያስ በመጨረሻ ባስተላለፉት መልእክት “ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ
የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋር አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሁናል
ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የሚያገለግሉበት ጥበብ መንፈሳዊ ከዕድሜና ጤና ጋር ይስጥልን።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
source: eotc-mkidusan.org
No comments:
Post a Comment