13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Saturday, December 3, 2011

በወርሐ ሕዳር የሚከበሩ በዓላት


ከቤተክርስቲያናችን አዋልድ መጻሕፍት ውስጥ በጥራዙ ትልቅ የሆነና በቤተክርስቲያን በዓመቱ ውስጥ የሚታሰቡትን እንዲሁም የሚከበሩትን በዓላት የሚያሳውቅ መጽሐፍ መጽሐፈ ስንክሳር ይባላል። ከዚህ ታላቅ መጽሐፍ ውስጥ በወርሐ ሕዳር ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የሚከተሉትን አቅርበንላችኋል። መልካም ንባብ!
ሕዳር 6 ቁስቋም
ጊዜው በ5 ዓ.ም ሲሆን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር አረማዊው ሔሮድስ ጌታችንን ሊገድለው በመፈለጉ በመልአኩ አሳሳቢነትና መሪነት ወደ ግብጽ ተሰዳለች። ምንም እንኳን ሔሮድስ 144000 ሕጻናትን የፈጀ ቢሆንም ሰው የሆነው አምላክ አምላክ ሲሆን ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን ግን አላገኘውም ነበር። እርሱ ግን   ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክን ይዛ ሳለ ለምክንያት ተሰደደች። 3ዓመት ከመንፈቅ ያህል በስደት ከቆየች በኋላ (ራእ.12፡1-6) ሄሮድስ ከክፋቱ የማይመለስ ቢሆን መልአኩ ሰይፈ መዓቱን መዞ ታይቶት ተልቶ ቆስሎ ሞቷል። ከዚህ በኋላ ዮሴፍን የሕጻኑን “የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ ( ማቴ.2፡20) ብሎት ከምድረ ግብጽ ወጥተው በረሀ በረሀውን ተጉዘው በዚህ ዕለት ደብረ ቁስቋም ገብተዋል።
ሕዳር 7 የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል
ጊዜው በ4ኛው ምዕተ ዓመት ሲሆን በዚህች እለት በዓል መሰራቱ ስለ ሁለት ነገር ነው፤ አንደኛው በሕይወተ ሥጋ ሳለ ንጉሡ ዱድያኖስ በረሀብ ይሙት ብሎ የምትልሰው የምትቀምሰው ከሌላት መበለት ቤት አስገብቶ ከምሰሶው ቢያስረው ምሰሶውን አለምልሞ ቤቷን በበረከት መልቶ ለልጅዋም ዕውረ ዓይን ጽቡሰ እግር ነበረና ፈውሶላታል። ሁለተኛው ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት ነው። የተሰራውም በአባት በእናቱ ቦታ ላይ ነው። ሥጋውንም ብላቴኖቹ ወደእዚያ አፍልሰውት ሕሙማንን ሲፈውስ ሙታንን ሲያነሳ ይኖር ነበር። ዲዮቅልጥያኖስ ሰይጣናዊ ቅንዓት አድሮበት አውህዮስን አጥፋ ብሎ ላከው። ቢሄድ ምዕመናን ለስዕሉ መብራት አብርተው ሲሳለሙት አገኘ። መብራቱን በሰይፉ ቆረጠው። ሳይታወቀው ስባሪው ከራሱ ላይ ወድቆ አቃጠለው። ሰውነቱ እንደሰነበተ አስክሬን ሸተተ። ሠራዊቱ በመርከብ ተሳፍረው ይዘውት ሲመለሱ ማዕከለ ባህር ሲደርሱ ሞተ። ከባህሩ ጥለውት ሄደዋል።
የሆነውን ነገር ቢነግሩት ሠራዊቱን አስከትሎ ሄደ። ከዓውደምህረት መንበሩን ዘርግቶ በትዕቢት ተቀምጦ ሳለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር መጥቶ ከነመንበሩ ገልብጦታል። በመንበሩ እጀታዎች የነበሩ ሁለት ዘንጎች ዓይኖቹን አውጥተውት ታውሮ ሠራዊቱም ትተውት ሄደዋል። እርሱም ከነዳያን ጋር እየለመነ በኃሳር ሞቷል።
ሕዳር 12 በዓሉ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
ጊዜው በ1528 ዓ.ዓ ገደማ ሲሆን ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ከምድረ ግብጽ እየመራ ማውጣቱን በማዘከር ነው። በያዕቆብ ልጅ በዮሴፍ ምክንያት እስራኤላውያን ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን ነግሶ አገዛዙን አጸናባቸው፤ ፍርድ አጓደለባቸው እስራኤላውያንም ለ430 ዘመናት በስቃይ ኖሩ። እግዚአብሔርም የራሔልን እንባና ልቅሶ ምክንያት አድርጎ ሙሴን አስነስቶ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ በ10 መቅሰፍት 11ኛ ስጥመተ ባህር እስራኤልን ከባርነት አውጥቷቸዋል።
ሕዳር 13 ሲመተ መላእከት
ሕዳር 16 ጾመ ነቢያት
ጾመ ነቢያት ጾመ ድኅነት ይባላል። ጾመ ነቢያት መባሉ ነቢያት በግዝረታቸው በመስዋዕታቸው መዳን የማይቻላቸው ቢሆን ለአዳም በሰጠው ተስፋ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ በሕማሙ በሞቱ ያድነን ብለው በየዘመናቸው ግብር ገብተው ቀኖና ይዘው አንስእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ ብለዋል፤ ጌታም የተናገረውን የማያስቀር ነውና አምስት ቀን ተኩል (አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን) 2ጴጥ. 3፡8 ሲፈጸም ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ እንደሰው አድጎ በ33 ዓመቱ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን አድኗልና ነው።  ጾመ ድኅነት መባሉም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፍቶ ድኅነት የተገኘበት ስለሆነ ነው። ይህ ጾም ከበዓለ ልደት አስቀድሞ ያሉትን ስድስት ሳምንታትን እንጾማለን።
ሕዳር 21 ጽዮን
እግዚአብሔር አምላካችን እስራኤላውያንን ከፈርዖን ቀንበር በተዓምራት ካወጣቸው በኋላ ሙሴ በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት ቆይቶ በእግዚአብሔር እጅ የተቀረጹ ሁለት ጽላቶችን
በውስጣቸው እስራኤላውያን እንዲመሩባቸው 10ቱ ትእዛዛት የተጻፉባቸውን ጽላት ይዞ ሲመጣ እስራኤላውያን አምልኮተ እግዚአብሔርን ትተው፤ ውለታውን ረስተው በጣዖት አምልኮት ቢያገኛቸው ከካህን እጅ መስቀል እንዲወድቅ ደንግጾ ጽላቱ ከእጁ ወድቆ ጣዖቱን ደምስሶታል። እግዚአብሔርም እንደቀደሙት ዓይነት ሁለት ጽላት ቀርጾ እንዲያመጣ ባዘዘው መሰረት ጽላቱን እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት ሰርቶ አቅርቧል፤ እግዚአብሔርም አሠርቱን ትዕዛዛት ጽፎበታል። ይህም የሆነው ለምሥጢር ነው የቀደመው ጽላት የአዳም ምሳሌ ሲሆን የመጀመሪያው ሰው አዳም በታላቅ ክብር ተፈጥሮ ሳለ ክብሩን ሕገ እግዚአብሔርን በመጣስ ወድቋል፤ ከክብር ቦታው ተሰዷል። ሁለተኛው ጽላት ምሳሌ ከሰው ወገን የሆነች በእግዚአብሔር የተመረጠች፤ ምክንያተ ድኅነት የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን የተጻፈው ቃል የቀዳማዊው ቃል ሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ የሆነው የጌታችን የመድኃኒታችን ምሳሌ ነው። (ዮሐ. 1፡1-3) ታቦተ ጽዮን 40 ዘመናት መናን ከደመና ውሐን ከጭንጫ እያፈለቀ በሠናይ መግቦት ምድረ ርስት አግብቷቸዋል፣ እግዚአብሔር በጽላቱ ላይ ያነጋግራቸው የልባቸውንም መሻት ይፈጽምላቸው ነበር።
ታቦተ ጽዮን በአፍኒንና ፊንሐስ በኃጢአት በካህኑ ኤሊ ቸልተኝነት ምክንያት ተማርካ በፍልስጤማውያን እጅ ከተማረከች በኋላ ፍልስጤማውያን አዛጦን ወስደው በቤተ ጣዖታቸው ከዳጎን ጋር አስቀመጧት። በማግስቱ ሊያጥኑለት ሊሰውለት ቢገቡ ዳጎን በታቦተ ጽዮን ፊት በግምባሩ ወድቆ አገኙት። ከቦታው መልሰውት ሄዱ። በሌላው ቀን ሲመለሱ እጅ እግሩ ተቆራርጦ ደረቱ ለብቻው ቀርቶ አገኙ ፤ ሰዎቹም በእባጭ ተመቱ። መቅሰፍቱ ቢጸናባቸው ወደጌት ወሰዷት። የጌት ሰዎችም እንዲሁ በመቅሰፍት ተመቱ። ወደ አስቀሎና ቢወስዷት “ልታስፈጁን ነው ወደ ሀገሯ መልሱልን” ብለው ጮሁ። ከሰባት ወር በኋላ  ወደ ሀገሯ ትመለስ ብለው ቀንበር ባልተጫነባቸው በሚያጠቡ ላሞች በሚሳብ አዲስ ጋሪ አድርገው የበደል መስዋዕት እንዲሆን በአምስቱ ከተሞቻቸው አምሳል አምስት የወርቅ አይጦች አድርገው ሰደዷት። ላሞቹ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሳይሉ ከኢያሱ እርሻ ደርሰው ቆመዋል። ታቦተ ጽዮንን ከሐውልተ ስምዕ አኑረው ሠረገላውን ፈልጠው ላሞቹን አርደው መስዋዕት አቀረቡ። ነገር ግን ሕዝቡ ታቦተ ጽዮንን በድፍረት በማየታቸው 5 ሺህ ያህሉ ተቀስፈዋል። ወስደውም በአሚናዳብ ቤት አድርገዋት ልጁ አልዓዛር 20 ዓመት አገልግሏታል።
 እግዚአብሔር ከበዓላቱ በረከትን ያድለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
 ምንጭ፡ ፍኖተ - ብርሃን መጽሔት በቦ/መ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት የሚዘጋጅ የወርሐ ሕዳር - ታሕሳስ /2004 ዕትም

Friday, December 2, 2011

“ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።” የማርቆስ ወንጌል 13፡33



መልዕክተ ፍኖተ - ብርሃን 
ዘቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት
 “ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።” የማርቆስ ወንጌል 13፡33
ይህን ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገረ ምጽዓቱን ነገር ከደቀመዛሙርቱ መካከል የሆኑት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብና እንድርያስ በጠየቁት ጊዜ የነገራቸው መለኮታዊ ቃል ነበር። በዓለም ላይ ሰው ተጠቦ የሚሰራቸው ስራዎችን ከደቀመዛሙርቱ አንዱ “መምህር ሆይ፥ እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው።” እርሱ ግን “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”ዮሐ.1፡3 የተባለለት አምላክ ነውና ይህን ምክንያት አድርጎ የመጨረሻው ዘመን ምን እንደሚሆን ነግሯቸዋል። ውድ ክርስቲያኖች የሚከተለውን የትንቢቱን ቃል አንብበን ጊዜያችንን እንመርምር፤
“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ። በዚያን ጊዜም ማንምእነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም። እነሆ፥ ከዚያ አለ’ ቢላችሁ አትመኑ፤ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።”
እግዚአብሔር ከመዓቱ ያድነን፤ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ከአጽራረ ቤ/ክ ይጠብቅልን። አሜን።
ምንጭ፡ ፍኖተ - ብርሃን መጽሔት በቦ/መ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት የሚዘጋጅ የወርሐ ሕዳር - ታሕሳስ እትም

Thursday, December 1, 2011

መልክዓ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።


“መቅድመ ኩሉ ንሰብክ ሥላሴ ፅሩየ፡ ከሁሉ አስቀድመን የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት እናስተምራለን።”  (ቅዱስ ቄርሎስ)
 

መልክዓ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

(በከሣቴ ብርሃን ማተሚያ ቤት በ1957 ዓ.ም  ታተመ። በድጋሚ በህዳር 1994 ዓ.ም በኢ.ዲ.ኤም ማተሚያ ቤት ታተመ።)






እሰግድ ለመለኮትከ እንተ ፈጠርከ ጽልመተ። እምቅድመ ትግበር ብርሃነ ወታስተባሪ መዓልተ። እግዚአብሔር አሐዱ እንተ ኢኮንከ ክልኤተ። በስምሰ ሰመዩከ ሠለስተ። እንዘ በመለኮት ዋኅድ ወብሑት አንተ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘሳረርከ ምድረ። ለዕጓለ እመሕያው ይኩን ወለእንስሳ ማህደረ። እግዚአብሔር ገባሬ እንበለ ትኅሥሥ መምክረ። ትፀውር ድደ በኃይልከ እንዘ ትነብር ጠፈረ። ወእንዘ ተሐንፅ መሠረተ ትፄአን ቀመረ።
እሰግድ ለመለኮትከ በኃይለ አርምሞ እንበለ ድምፅ። ለጠባይዓ ማይ አምጻእኮ እምኀበ ኢምንት አንቀጽ። እግዚአብሔር ርቱዕ ዘኢታደሉ ለገጽ። ፍታኅ ሊተ እግዚኦ እምነ እኩያን አብያጽ። ወተበቀል በቀልየ በግሩም ተግሣፅ። 

እሰግድ ለመለኮትከ ፈጣሬ እሳት ውዑይ። እንበለ እሳት ካልዕ ውስተ ከርሰ ቁሪር ቀላይ። እግዚአብሔር አብ እንተ ተአቅብ በማይ። አዳም ግብርከ እግዚአ ወኩሉ ሠናይ። በኀልዮቱ እትፌሣህ ገብርከ ነዳይ። 

እሰግድ ለመለኮትከ እንተ ፈጠርከ ነፋስ። ወቦቱ ገበርከ ለጠባይዓ ማይ ቅዱሰ። እግዚአብሔር ምዕረ ካዕበ ወስልሰ። አስተንፍስ ውስተ አፉየ መዓዛ ሕይወት ሐዲስ። እም ሕማመ ሥጋ ወነፍስ ዘይከውን ፈውሰ።
እሰግድ ለመለኮትከ ገባሬ መላእክት እምተደሞ። ወምሳሌሆሙ አዳም እንበለ ነቢብ ወአርምሞ። እግዚአብሔር ኃይልየ ወሐዳፌ ነፍስየ እምተሰጥሞ። ድካምየ ትፁር ኂሩትከ ወለልብየ ሕማሞ። ከመ ወላዲቱ ለወልዳ ትፀውር ድካሞ።
እሰግድ ለመለኮትከ እንተ ፈጠርከ ቀዳሚ። ሰማየ አርያም ኅቡዓ እምባሕርየ ምስጢር ኢተተርጓሚ። እግዚአብሔር በእሁድ ወጣኔ ፍጥረት ወፈጻሚ። እስዕን ፈክሮተከ በሕሊናየ ቀዋሚ። ወኢይትከሃሎ ለአፉየ ባሕርየከ ይስሚ።
እሰግድ ለመለኮትከ ለራዕየ ኅቡዓት እለ ተፈጥሩ። ጠፈረ ይኩን ዘትቤ ወይጻእ እማኅደሩ። እግዚአብሔር ለከእስከነ መላእክት ገረሩ። ዲያብሎስ ወድቀ አሜሃ እምሕሊናከ መንበሩ። ወመንገለ ኃሣር ወረደ እምክብሩ።
እሰግድ ለመለኮትከ በሰዓተ ሌሊት ዘሰኑይ። ጠፈረ ይኩን ዘትቤ እንዘ ትከፍሎ ለማይ። እግዚአብሔር እምኀበ አልቦ አምጻኤ ሰመንቱ ባሕርይ። ምድረሰ አንበርከ ዲበ ባሕር ዐባይ። አመ ከመ ቀመር ሰቀልኮ ለልዑል ሰማይ።
እሰግድ ለመለኮትከ ዘአስተጋባእኮ ከመ ዝቅ። ለማየ ውቅያኖስ ግሩም ኀበ ምዕላዲሁ ዕሙቅ። እግዚአብሔር ሠራዒ ቀዳሜ ቃልከ ጽድቅ። አስተርአየት የብስ ሶቤሃ በትርሲተ ጽጌ ጽፉቅ። እምዕለተ ዕሁድ ፀዳል በሠላስ ሠርቅ።

እሰግድ ለመለኮትከ ከመ ቅጽበተ ዓይን ዘፈፀመ። አስተጋብኦ ማይ ስፉህ ድኅረ ዓለመ አስጠመ። እግዚአብሔር ከሃሊ እንተ ትገብር መድምመ። እም አይቴ ወጠንከ አሜሃ አመ ፈጠርከ ዓለመ። ወኀበ አይቴ ረሰይከ ውሳኔ ወአቅመ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘአሰርጎካ ከመ ልብስ። እምድኅረ ዕለታት ክልዔቱ በዕለት ሠላስ። እግዚአብሔር ለምድር በሥነ ጽጌያት ሐዳስ። አስተራእየት ጽጌ ሶቤሃ ውስተ ምድረ ሐጋይ ወየብስ። በገራኅተ ሥጋ ወነፍስ ማርያም በለስ።

እሰግድ ለመለኮትከ ለዘበኂሩቱ በቆሉ። ዘመደ ዕፀዋት በሳዕር መግቦተ ሥጋ ዘይክሉ። እግዚአብሔር ኪያከ እለ ውስተ ታሕቱ ወላእሉ። ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ይብሉ። እስመ በትእዛዝከ ኮኑ ወተፈጥሩ እሉ።

እሰግድ ለመለኮትከ እንተ ተክለ በምስራቅ። ኤዶምሃ ገነተ ተድላ ወጽድቅ። እግዚአብሔር መታሪ ወገባሬ ነገር ሕሉቅ። ትሳረር ዲበ ማይ ወተሐንፅ በደቃቅ። ወትጠበልሎ ለግብር በጊሜ ረቂቅ።

እሰግድ ለመለኮትከ በዕለተ ረቡዕ ዘአርአየ። መንገለ ምዕራብ ወርኃ ወመንገለ ምስራቅ ፀሐየ። እግዚአብሔር {ፃ እንተ ትዌስን ቀላየ። ትኤምድ በነፋስ እንዘ ተዓርግ እምዝየ። ትሰቅል ማየ ወትሰሚ ሰማየ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘለሊከ ሳረርከ። እምነ ብርሃን ወነፋስ ዘከዋክብት ፈለከ። እግዚአብሔር ኀበኒ ዲናረ ተደሞ ብሩከ። በኁልቆ ዐሰርቱ ሰዓት ለዘተቀነይኩ ለከ። ምስለ እለ ፃመው ነግሃ እስከ ይከውን ሰርከ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘገበርከ ወርኃ በዕድሜሁ። ፀሐይኒ አእመረ ምዕራቢሁ። እግዚአብሔር ሌሊተ ዘታመጽእ በበጊዜሁ። ወቦቱ ይፃዑ አራዊተ ኀበ ገደላ ላህ በበዝኁ። እምከመ ሰረቀ ፀሐይ የአትው ናሁ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘፈጠረ አመ ሐሙስ። እምርጥበተ ማይ ዓሳተ ወእምነ ቆሪር የብስ። እግዚአብሔር ስፉሕ ረቂቀ ጠባይዕ እምነፋስ። እንተ ትሴባህ በውስቴታ ከመ ቤተ ፀሎት ንዑስ። እስመ ርኅበ ሰማይ ወምድር አሐቲ መቅደስ።

እሰግድ ለመለኮትከ ፈጣሬ ንዑሳን ዘይትሐወሱ። ወገባሬ እንስሳ ዓበይት በባሕረ ውቅያኖስ ማዕከለ ከርሱ። እግዚአብሔር ክድነኒ በአክናፈ ኪሩቤል ስሱ። ኢያደንግፀኒ አርዌ እንተ ይበርቅ ጢሱ። ወጽንፈ ዘነቡ ውዱደ ያሰምክ በርእሱ።

እሰግድ ለመለኮትከ እንተ ወሀብካሁ ለምስካብ። ለግሩም አርዌ ሳብዕተ እደ ማይ ርጡብ። እግዚአብሔር አሐዱ ፈጣሬ ዓለማት ዘዓርብ። ድኅረሰ ትመትሮ በሥልጣንከ ዕፁብ። ግዝፈ ፍጥረቱ ያንክሩ እለ ርእዩ ሕዝብ።

እሰግድ ለመለኮትከ በዕለተ ሰዱስ ዘፈጠረ። አባግዓ ብሔር ኩሉ ወእንስሳ ገዳም ኅቡረ። እግዚአብሔር ሎሙ ዘየአክሎሙ ሳዕረ። አስተዳሎከ ሲሳዮሙ እስከ ታመጽኦሙ ድኅረ። እስመ ከማሁ ለኩሉ ታስተዴሉ ወትረ።

እሰግድ ለመለኮትከ እምቀለመ መሬት ፀዓዳ። ዘአካለ አዳም ሰዓልከ ወለካዕከ ውስተ ሰሌዳ። እግዚአብሔር ትቤ አመ ዕለተ ዓርብ ብዝኅተ ዕዳ። ንግበር ሰብአ በአርያነ እነግዳ። መልክዓ ልቡና ውእቱ ወአኮ አነዳ።

እሰግድ ለመለኮትከ እምገቦ አዳም ድኅረ። እንተ አውፃዕካ ለሄዋን ከመ ትርድዖ  ተግባረ። እግዚአብሔር ኪያከ በዘአፀመድከ ወትረ። መኑ ያወፅእ እምልብየ ፍትወተ ዓለም ነኪረ። እንበለ ጥበብከ አምላካዊ ዘሰማየ ገብረ።

እሰግድ ለመለኮትከ ዘአእረፎሙ ለአይሁድ። በዕለተ ሰንበት ሳብዒት እምተግባረ አእጋር ወእድ። እግዚአብሔር አብ ሰንበተ ክርስቲያን አሁድ። አግዕዘኒ እምቅኔ ሥጋ ለአብጽሖ ንሰቲት ሰጊድ። ኀበ ኁልቆ ዕሥራ ወክልኤቱ ስሙያን አንጋድ።

ስብሐት ለእግዚአብሔር ለለሰርቀ ዕለተ ወለያልይ።      ስብሐት ለእግዚአብሔር በተባርዮ ክረምት ወሐጋይ።   ስብሐት ለእግዚአብሔር በወርኀ መፀው ወፀደይ።      ስብሐት ለእግዚአብሔር በኁልቆ ኩሉ ዘኢይትረዓይ።   ስብሐት ቅድምናከ ወትረ ይነግር ሰማይ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሠማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለእለትነ ሃበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመንኅነኒ ንህድግ ለዘአበሰለነ ኢታብዓነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሀነ እምኩሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግስት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

በሠላመ ቅዱስ ገብርኤል መልዓክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሠላም ለኪ ድንግል በህሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሠላም ለኪ ቡርክት አንቲ እምአንእስት ወብሩክ ፍሬ ከርስኪ ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕተ ፀጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ ሰዓሊ ወጸልዪ ምኅረተ ለነ ሀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይስረይ ለነ ኃጣውዒነ።

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ይዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም። አሜን። 

የቦ/መ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት