በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሰዎች ፈረዱብኝ
ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ (2)
አምላኬ ሆይ ተመስገንልኝ ጌታዬ ሆይ ተመስገንልኝ ሌላ ምን ቃል አለኝ
ሊያልፉኝ አልወደዱም ነቄን ሊሰውሩ
ሰዎች ፈጠኑብኝ በደሌን ሊያወሩ
አንተ ግን ሰብስበህ በፍቅር ሸፈንከኝ
ይህ ፍቅርህ ሰበረኝ አጣበቀኝ ካንተ
ደጅህ ያመጣኛል ሁሌ እየጎተተ (2)
መርከሴን አውጀው ሲያነሱብኝ ድንጋይ
ሰወረኝ ተዓምርህ ልጅ ሳልሰቃይ
ወደህ ስለማርከኝ ብዙዎች ተከዙ
ይህ አይደለም ብለው የኃጢአት ደሞዙ
ካነተ በላይ ጌታ ማን ሊያውቀኝ ይችላል
የፍቅርህን ሚዛን ማንስ ያዛባዋል (2)
ሰወረኝ ተዓምርህ ልጅ ሳልሰቃይ
ወደህ ስለማርከኝ ብዙዎች ተከዙ
ይህ አይደለም ብለው የኃጢአት ደሞዙ
ካነተ በላይ ጌታ ማን ሊያውቀኝ ይችላል
የፍቅርህን ሚዛን ማንስ ያዛባዋል (2)
ማዳንህ ይደንቃል ለወደኩት ልጅህ
ምህረትህ ይደፋል ሁሌ በሚዛንህ
እንደሰው አይታይ ፍርድህም ይለያል
ለባርያህ አርነት በምህረት ፈርደሃል
ፍቅር እየዘረዘርክ መንገዴን የጠረክ
ስለልጅህ ጽድቅን በምህረት የፈረድክ (2)
እኔ አልፈርድብህም በሰላም ሂድ አልከኝ
ዳግም እንዳልበድል በፍቅር እያየኸኝ
ወደፍቅርህ ህጎች ነፍሴን አፈዛለሁ
እንዲህ ከወደድከኝ ወዴት እሄዳለሁ
አልለይም ካንተ ከፍቅር መድረኬ
አመልካለሁ አንተን ፊትህ ተንበርክኬ (2)
ዳግም እንዳልበድል በፍቅር እያየኸኝ
ወደፍቅርህ ህጎች ነፍሴን አፈዛለሁ
እንዲህ ከወደድከኝ ወዴት እሄዳለሁ
አልለይም ካንተ ከፍቅር መድረኬ
አመልካለሁ አንተን ፊትህ ተንበርክኬ (2)
“የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው ለዘላለም ይኖራል የእግዚአብሔር
ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።” መዝ. 19፡9
ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።” መዝ. 19፡9
No comments:
Post a Comment