ይድረስ ለፈጣሪ መንበረ ጸባዖት
ከትልቁ ሥፍራ ከሰማዩ መንግሥት
ፍርድ ሳይዛነፍ ከሚፈጸምበት፡፡
ላኪው በምድር ላይ ግፍ የደረሰብኝ
ጐስቋላ አገልጋይህ ደካማ ባሪያህ ነኝ፡፡
ሳጥናኤል የሚሉት የቀድሞ ጠላቴ
ፍርድ ሳይዛነፍ ከሚፈጸምበት፡፡
ላኪው በምድር ላይ ግፍ የደረሰብኝ
ጐስቋላ አገልጋይህ ደካማ ባሪያህ ነኝ፡፡
ሳጥናኤል የሚሉት የቀድሞ ጠላቴ
ቂሙን ሳይዘነጋ እንደ አዳም አባቴ
ከገነት ሊያስቀረኝ ቀጥቅጦ ጥሎኛል።
ከመርዘኛው ባሕር በቁሜ ዘፍቆኛል።
በአፍና አፍንጫዬ ደግሞም በጆሮቼ
በአፍና አፍንጫዬ ደግሞም በጆሮቼ
መርዙ ተጠቅጥቆ በየአካል ክፍሎቼ
አውጣኝ እያልኩህ ነው እባሕር ገብቼ፡፡
ለመታገል ሞከርኩ ከእጁ አልወጣሁም።
ደካማ ነኝና በፍፁም አልቻልኩም።
ፍርድ ሰጭው ዳኛ ችግሬን ቃኝተኸው
መፍትሔ እንድትሰጠኝ ወዳንተ እጮኻለሁ፡፡
መፍትሔ እንድትሰጠኝ ወዳንተ እጮኻለሁ፡፡
ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን 1986 ዓም
/በሐመር መጽሔት ለንባብ የዋለ/
Source: http://kesisyaredgebremedhin.blogspot.com
No comments:
Post a Comment