13

.

"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው::" የማቴዎስ ወንጌል 7: 4

"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅናወተት ግዙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 55 : 1

Monday, November 21, 2011

ስድስተኛው ችንካር


ሕማሙ …
ከአምስቱ ቅንዋት ሕመሙ የጸና አጥንት የሚሰብር
እጅግ የበረታ ጎንን ከሚወጋ ከሌንጊኖስም ጦር
ከመጻጻ ሐሞት አብዝቶ የሚመር ፤


በጣሙን የከፋ
ከአይሁድ ዘለፋ
ከጭፍሮች ገፈፋ፤
ከጴጥሮስ ክህደት ከቶማስ ጥርጥር ከሾህም አክሊል በላይ
ኃያል ነው ሕመሙ እስትንፋስ የሚስያስቀር ከልብም የሚለይ

ቸንካሪው …
የአምላኩን ውለታ ቤዛነቱን ረስቶ
ከርሱ ርቆ የሚኖር በደልን አብዝቶ፣
በደም የተገዙትን የሚያወጣ ገፍቶ
ከቃል የተጣላ በአርዮስ ክህደት ጸንቶ
ከአባቱ የሚያሳንሰው ከመንፈሱ ለይቶ::
ሌላ ማንም አይደል እርሱ ነው ይወቀው
 በስድስተኛው ችንካር ጌታውን ቸንካሪው::
ማስረሻዬ  ወርቁ
Source: www.bahiran.org

No comments:

Post a Comment